|
ወደ አዱሊስ ኢንተርፕራይዝስ ድኅረ-ገጽ እንኳን በደህና መጡ::
አዱሊስ ኢንተርፕራይዝስ የሰነድና የአፈ-ቃል ትርጉም ሥራዎች፣ የኮፒ፣ የኅትመትና ማናቸውንም የጽህፈት ሥራአ አገልግሎት በመስጠት ዕውቅናን ያበረከተ ድርጅት ነው።
ባልደረቦቻችን ከአርባ ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ ያካበቱ በቋንቋና ሥነ-ጽሁፍ ከፍተኛ ዕውቀት ያዳበሩ ስለኾኑ አገልግሎታችን በሰዓቱ ኪስዎን ሳያራቁት በትኅትና የሚሰጥ ነው።
የኢሚግሬሽን ሆነ የዶክተር ቀጠሮ ካለብዎት፣ ፍርድ ቤት ከተጠሩ፤ለስብሰባዎችና ሌሎችም የአስተርጓሚን ዕርዳታ ለሚጠይቁ ሂደቶች ሁሉ ከተፍ ብለን በመገኘት ብርቱዕ አንደበት፣ በሚገባ ቋንቋና ምስጢር በጠበቀ ሁኔታ እናገለግልዎታለን።
አስተርጓሚዎቻችን በቋንቋዎት አፋቸውን የፈቱ፣ ከዚያም አልፈው በተለያዪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ቋንቋውን ያጠኑት በመሆናቸው በሙሉ ልብ ሊተማመኑብን ይችላሉ።
ከአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛና ሌሎችም ሃገራዊ ቋንቋዎች በተጨማሪ አረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ጀርመንኛና የመሳሰሉትን ባጠቃላይ ወደ ፩፰፯ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች አቀላጥፈው የሚናገሩ አስተርጓሚዎቻችን ከትርጉም እስከ አጠቃላይ የመገናኛ ሥልት ማማከር ድረስ ሊያገልግልዎት ተዘጋጅተዋልና ፍላጎትዎን ያማክሩን ።
|